“የብድርና ቁጠባ ተቋም ወረቴ ነው፣ በሰው ሃገር ሂዶ ከመቀጥቀጥ ተግቶ ከሰሩ ሃገራችንም ዱባይ ናት” ወ/ሮ ሉባባ ኢብራሂም ሰይድ (በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድርና ቁጠባ ተቋም የባምባሲ ቅርንጫፍ ደንበኛ)
በደርግ ዘመን የ7ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩ፣ የልጆች እናት የሆኑ፣ በምግብ አብሳይነት የሰው ቤት ተቀጣሪ የነበሩ፣ የባልትና ሙያ ያላቸው፣ ልጆች ለማሳደግ 8 ዓመት በረሃ የተንከራተቱ፣ መኪና የመግዛት ህልም ስላላቸው ወደ አረብ ሃገር ሊሄዱ ሂደት ጀምረው በደላላ ቤት ሲንከራተቱ የነበሩ፣ ከ20 ሺ ብር ጀምሮ በተከታታይ ዙሮች እስከ 500 ሺ ብር ብድር በመውሰድ የባምባሲ ቅርንጫፍ የግል ብድር ደንበኛ የነበሩ፣ በባምባሲ ወረዳ መለስተኛ የሆቴል ስራ (በተለይ ምግብ) ላይ የተሰማሩ ታታሪ ሰራተኛ የሆኑ፣ በወር ከፍተኛ ገንዘብ መቆጠብ የቻሉ፣ በ1.3 ሚሊዮን ብር የህዝብ ማመላለሻ አባዱላ የገዙ፣ በ50 ዓመታቸው ማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሆኑ ብርቱ እማወራ ናቸው፡፡
ወ/ሮ ሉባባ ኢብራሂም ሰይድ ሲናገሩ በ1.3 ሚሊዮን የገዙት መኪና በአሁ ሰዓት ከ2.7 ሚሊዮን ብር በላይ አቅም አለው፡፡ “አባዱላ መኪናዬ ሰባት ወር እንደሰራልኝ 2 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ ብር እንድሸጥ ተጠይቄያለሁ፡፡ ግን አልሸጥም ጊዜው አሁን ስላልሆነ፡፡ መሸጥም ካለበት በቅድሚያ መኪናው ሌላ መኪና መውለድ አለበት፡፡ ትልቁ ነገር ደግሞ ይህን 2 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ ብር ብድርና ቁጠባ እንደሰጠኝ ነው የምቆጥረው፡፡ ተቋሙ ባያስጀምረኝ ይህ ብር ለእኔ ህልም ነበር፡፡ ወላሂ ይህ ተቋም ወረቴ ነው፡፡ አሳድጎኛል፡፡ ብር ለመበደር ሲያስቡ መጀመሪያ ሰርቶ መቆጠብን የተማርኩት ከእነሱ ነው፡፡ እኔም ህይወቴ እስካለ ድረስ ሰርቼ እንዲያልፍልኝ ነው የምፈልገው፡፡ ከተቋሙ ባለመራቄ እጅግ ተጠቅሜለሁ፡፡ ዘወትር እየሄድኩ ምክር እቀበላለሁ፡፡ ትንሽም ይሁን ትልቅ በየጊዜው እቆጥባለሁ፡፡ ዕዳ የምከፍለውም አንድ ቀን እንኳን ሳላዘገይ ነው፡፡ እኔ በአጋጣሚ በማልኖርበት ጊዜ የብድር መክፈያን ቀን ወር በገባ በ16ኛው ቀን መሆኑን ልጆቼ ያውቁታል፡፡ ይከፍላሉ፡፡
ለብድርና ቁጠባ ተቋም እና ሰራተኞቹ የማመስገኛ ቃላት የለኝም፡፡ እኔ የተሻለ የምለውን ኑሮ እየኖርኩ ከሃብታሞቹ ጋር ዕቁብ እየጣልኩ ነው። ልጆቼ ሲመጡ “የእማ ቤትኮ አረብ ሃገር ነው” ይሉኛል።ስራ ይበዛል ማለታቸው ነው። ብዙ ዕቅድ አለኝ ገና ብዙ ሰሪቼ ፈርሃ ሆኜ መኖር እፈልጋለሁ፡፡”
“ከ500 ብር ጀምሮ በዕቁብ መልክ በቡድን በቆጠብነው 50 ሺ ብር ዋስትና ተነስተን ዛሬ ባለ-ሃብት እየተባልን ነው፡፡ አልሃምዱሊላህ ከዚህ በላይ እናድጋለን፡፡ ህብረተሰቡ ሲጠቀም እንደወጣት እኛም እናድጋለን፡፡” አቶ ሁሴን አልሂሰን (በኡራ ወረዳ የባሻቡዳ ቀበሌ ነዋሪ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድርና ቁጠባ ተቋም የአሶሳ ቅርንጫፍ ደንበኛ)
ቀደም ሲል በሹፍርና ሙያ ይተዳደር የነበረ፣ 50 ሺ ብር ቆጥቦ ከ250 ሺ ብር ጀምሮ የአሶሳ ቅርንጫፍ የቡድን ብድር ደንበኛ የሆኑ፣ በወሰዱት ብድር ስርተው የእርሻ ትራክተር እና የእህል ወፍጮ ባለቤት የሆኑ፣ በአሁኑ ሰዓት በቀን ከ18 በላይ ሰራተኛ የሚያሰራ 5 ዓባላት ያሉት አልሂሰን፣ መሪየምና ጓደኞቹ የሚባል የእርሻ ስራ ማህበር ያደራጁ ናቸው።
“የስኬታችን ሚስጥር ፅናትና ብርታት ነው፡፡ ብድሩን ለጫት፣ ለሲጋራ፣ ለጠላ ቤት አላዋልነም፡፡ የስራ እንጂ የሻይ ሱስ እንኳን የለብንም፡፡ ማህበራችንን አልበተንነም፣ ገንዘብ አልተከፋፈልነም፣ ወጪ እንጂ አስተማማኝ ገቢ የለለውን ሞተር ሳይክል እንኳን አልገዛንበትም፡፡ እኛ የገዛነው የግብርና ግብዓት ነው፡፡ ከዚያም በ20 ሺ ብር ትራክተር ተከራይተን 8 ሄክታር አለማን፡፡ በ8 ሄክታር ያለማነው ፍሬ ሲያፈራ ትራክተር ገዛን፡፡ የወሰድነውን ብድር ለስራ ዓላማ ነው ያዋልነው፡፡ የማህበረሰባችን ጥያቄ የነበረው የዕህል ወፍጮም ገዝተን አገልግሎት እየሰጠ ነው።
በመጀመሪያ ዙር ትራክተር ገዝተናል፡፡ በገዛነው ትራክተር በዚህ ዓመት በ17 ሄክታር ላይ ያመረትነው አኩሪአተር፣ በቆሎ፣ በርበሬ፣ ማሽላ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ ነው፡፡ ከበርበሬ ምርት ብቻ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ገቢ እንጠብቃለን፡፡ አልሃምዱሊላህ በደንብ ነው ያፈራልን፡፡ ማሽላ በ8 ሄክታር ላይ ዘርተናል፡፡ ከዚህም ከ400 ኩንታል በላይ እንጠብቃለን፡፡
ወጣቱ ጫት፣ ሺሻ፣ ሲጋራ መተው አለበት፣ የቀደሙት በተለይም ወላጆቻቸው የሚናገሩትን መስማት አለባቸው፡፡” ( አቶ ሁሴን አልሂሰን የማህበሩ ሊቀመንበር)
+3
All reactions:
88Guteta Birhanu, Amuna Asemani and 86 others
“ከጭቃ ውስጥ ወርቅ አግኝተናል፤ በ2016 -17 ዓ.ም የፕላስቲክ መልሶ ማምረቻ ቴክኖሎጂ (ኢንዱስትሪ) ወደ ክልሉ ለማስገባት ዕቅድ አለን፡፡” አቶ ጀምበሩ ተሰማ።
ስራ ለመጀመር ከሰባት ዓመታት በላይ በዕቅድና ጥናት ላይ የነበሩ፣ የማህበሩ ዓባላት ተምረው ተመርቀው ለዓመታት ስራ አጥ የነበሩ፣ “ጀንበሩ፣ ዮዲትና ጓደኞቻቸው” ኢንተርፕራይዝ በአሶሳ ከተማ ያደራጁ፣ በ2013 ዓ.ም በ500 ሺ ብር የቡድን ብድር ስራ የጀመሩ፣ በተለምዶ “ቁራሊዮ” በማሰባሰብ እና አጥቦ በመፍጨት ለእንደገና ማምረት (RECYCLING) ዝግጁ አድርገው ወደ አዲስ አበባ የሚልኩ፣ አሁን ላይ የቀን ሰራተኞችን ሳያካትት በኮንትራት የሚሰሩ 12 ሰራተኞችና እስከ አምስት ሺ ብር ወርሃዊ ተከፋዮች 6 ቋሚ ሰራተኞች ያሏቸው ናቸው።
“ስራ ማጣት ከባድ ነው፡፡ ስራን መፍጠር ደግሞ ብልጠት ነው፡፡ ፍላጎትና አቅም ከሃሳብ ጋር ኖሮ በገንዘብ ዕጥረት ምክኒያት ስራ አጥ መሆን ቀላል አይደለም፡፡ ሰው ከሃሳቡ መሞት የለበትም፤ ይልቁንም ሃሳቡን ወደ ተግባር ለመቀየር መፍጨርጨር አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ ልማታዊ የሆነ ዓላማ እንዲኖራቸው ለወጣቶች ይህንን ብዙ ጊዜ ነው የምናገረው፡፡ እኛ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ የቆየን ቢሆንም ከማይጠቅም ጭቃ ውስጥ ማለትም ማህበረሰቡ ተገልግሎ ከሚወረውረው ቆሻሻ ውስጥ ወርቅ አይተናል፡፡ ለዚህም የብድር እና ቁጠባ ተቋም ለስኬታችን ትልቅ ሚና የተጫወተ ባለውለታችን ነው፡፡
ሰው በተለይም ወጣቱ ከውድቀት መማር አለበት፡፡ ድሮም ቢሆን የማይሰራ፣ የማይሞክር፣ የማይፈተን አይወድቅም፡፡ የሚወድቅ ሰው የተፈተነ ነው፡፡ ፈተና ከለለ መውደቅ አይኖርም፡፡ መውደቅም ከለለ መነሳት አይኖርም፡፡ ብዙ ወጣት በትንሽ ሙከራ ተስፋ ይቆርጣል፤ በዚህም ወደ መከረኛ መደበቂያ (ሱስ) ይሄዳሉ፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ከራስ አልፎ ለሌሎች ለመትረፍ ምረን ከመሆን ዕይታን ማስፋት፣ ሃገርንና በተሰቡን እንዲሁም ራሱን መውደድ ያስፈልጋል፡፡ እኛ ራዕያችን ትልቅ ነው፡፡ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም አስፈላጊ አማራጮችን ተጠቅመን በ2016 ዓ.ም Recycle machine ከቻይና እናስመጣለን፡፡ በ2017 ዓ.ም ቅርንጫፎቻችንን በክልሉ አስፍተን ይህንን ስራ ወደ ትልቅ ኢንዱስትሪ ቀይረን ወደ አዲስ አበባና የውጭ ሃገራት የምንልከውን ጥሬ እቃ አስቀርተን እዚሁ ምርቱን እናመርታለን የሚል ዕቅድ አለን” አቶ ጀምበሩ ተሰማ (የማህበሩ ሊቀመንበር)
በ2022/23 እ.አ.አ 414.49 በላይ ቁጠባ በማሰብሰብ ከ 516.3 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር በማሰራጨት በብሄራዊ ባንኩ ስታንዳርድ መሰረት ብድር ለማስመለስ እንደሚሰራ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም የአሶሳ ዲስትሪክት አስታወቀ፡፡
የአሶሳ ዲስትሪክት በአሶሳ ከተማ እና የመተከል ዲስትሪክት በግልገል-በለስ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የ2021/22 እ.አ.አ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2022/23 እ.አ.አ የዕቅድ ማናበብ መድረክ ተጠናቋል፡፡
25-12-2014 ዓ.ም
አሶሳ
የብድር ጥራትን ለማስጠበቅ በደንበኛ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ እና ከአካባቢው የሥራ ባህል ጋር የሚዛመዱ እና ለተቋሙም ሆነ ለደንበኛው ውጤት ማምጣት የሚችሉ አዳዲስ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎቶችን በመቅረጽ በ2022/23 እ.አ.አ 414.49 በላይ ቁጠባ በማሰብሰብ ከ516.3 ሚሊዮን በላይ ብድር በማሰራጨት በብሄራዊ ባንኩ ስታንዳርድ መሰረት ብድር ለማስመለስ እንደሚሰራ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም የአሶሳ ዲስትሪክት አስታወቀ፡፡ ዲስትሪክቱ በ2022/23 እ.አ.አ 112.99 ሚሊዮን አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት ብዙአየሁ እንደተናገሩት የማስፈፀም አቅም ግንባታ፣ የደንበኞች ውጤታማነትን ከምልመላ ጀምሮ በመከታተል፣ ብድርን በቁጠባ ለመሸፈን የሚያስችል ሰፊ ስልት በመንደፍ የብድር ስርጭትን በማስፋት፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር፣ ለእስላሚክ ፋይናንሲንግ አገልግሎት እና ለኮር-ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት በመስጠት በዲስትሪክቱ በዘርፉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አመላክቷል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ም/ ዋና/ ስራ አስፈጻሚ አቶ አድጎ አምሳያ እንደተናገሩት የዲስትሪክቱ ቅርንጫፎች ከፍተኛ የአምራችነት አቅም ያላቸው በተለይም በማዕድን ምርት፣ እርሻ፣ እርባታና ማድለብ፣ የንግድ ሥራ፣ የእንጨት ሥራ፣ ብረታ ብረት ሥራ፣ ምግብ ዝግጅት፣ ኮንስትራክሽን ላይ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በጥንቃቄ በመለየትና ከፍተኛ የፍላጎት ቁጠባ በማሰባሰብ ጥራት እና ተደራሽነት ያለው የብድር ስርጭትን ማስፋት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በሶስቱም ዲስትሪክቶቹ በመታገዝ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎቶችን በማቅረብና የደንበኞችን ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በአጠቃላይ 213.92 ሚሊዮን ብር ገቢ ያገኛ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ተቋሙ አሁን ያለውን 624.9 ሚሊዮን አጠቃላይ ሃብት ወደ አንድ ቢሊዮን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፡፡
በተቋሙ በ2021/22 እ.አ.አ በሁሉም ዲስትሪክቶች በቁጠባ አሰባሰብ፣ ብድር ስርጭት፣ ብድር አመላለስ፣ የውዝፍ ብድር አስተዳደር መሰረታዊ መስፈርቶች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የሸርቆሌ፣ የዳንጉር፣ የኡንዱሉ እና አሶሳ ቅርንጫፎችን በመለየት ዕውቀናና ተጨማሪ የገንዘብ ማበረታቻዎችንም ያበረከተ ሲሆን የአሶሳ ዲስትሪክት ቅርንጫፍ ሰራተኞች የተቋሙ ከፍተኛ የስራ አስፈጻሚ አካላት የዋና መ/ቤቱን የህንፃ ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡
+7
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ማኔጅመንት፣ የአሶሳ ዲስትሪት እና የቅርንጫፎቹ ስራ አስኪያጆች የአመራር እና የደንበኛ አያያዝ ክህሎት ስልጠና በቢዝነስ ደቨሎፕመንት እና ሪሰርች ስራ ክፍል በመታገዝ ሰሞኑን ወስደዋል።
የተሻለ የአመራር ቁርጠኝነት በማስፈን፣ አውንታዉ የአመለካከት ለውጥ በማምጣት፣ የዳበረ የባለቤትነት ስሜት በማጎልበት፣ የተሻለና ዉጤታማ የደንበኛ አያያዝ በማስፈን የላቀ የጋራ ዉጤት ከማስመዝገብ አኳያ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት ስልጠናው የሚያግዝ ነው ተብሎ ይጠበቃል።
በየደረጃው ያላችሁ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ሁሉም ስራ አስኪያጆች የ2022/23 ዓመታዊ የስራ እንቅስቃሴ ሪፓርታችሁን ከማስተቸት እና አዲስ አመታዊ ዕቅዳችሁን ከመቀበል ጎን ለጎን የሁላችንም የስራ ውጤት የሆነውን የዋና መ/ቤት የህንፃ ግንባታ ሂደት ስለጎበኛችሁ እናመሰግናችኋለን። በጉብኝታችሁ ወቅት የሰጣችሁን ገንቢ አስተያየት እና የተሰማችሁ ልባዊ ደስታ ለሁላችንም ለነገው የተቀናጀና የተሻለ ስራ ስንቅ ነው።
ተቋሙ ለደንበኞቹ እና ለሰራተኞቹ አስተማማኝ እና ምቹ የአገልግሎት መስጫ እና መቀብያ ቦት በሁሉም ቅርንጫፎቹ የማመቻቸት ግዴታ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት የረጅም እና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያለው ስለሆነ ወደ ፊት እናንተም አገልግሎት በምትሰጡባቸው አከባቢዎች ወጥ በሆነ ዲዛይን መለስተኛ ግንባታዎችን መስራት የሚያስችል አቅም የመፍጠር ጉዳይ ላይ ትኩረት እንድታደርጉ አደራ ማለት እንፈልጋለን።
ዓመቱ የስኬት ይሁንልን!