ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች

ራዕይ

  • ልማታዊ አመለካከቱ የላቀ፣ በብድር አጠቃቀሙ ውጤታማ የሆነ፣ የቁጠባ ባህሉ የዳበረ፣ ከድህነት የተላቀቀ እና  በእራሱ የሚተማመን ደንበኛ (ዜጋ) ማየት  ነው ፡፡

ተልዕኮ

  • በዝቅተኛ እና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ አምራች የህብረተሰብ ክፍሎች በዘላቂነት የብድርና የቁጠባ አገልግሎት አግኝተው ኢኮኖሚያዊ ገቢያቸው እንዲያድግ፣ ኑሯቸው እንዲሻሻል ብሎም ድህነት እንዲቀረፍ ማገዝ ነው፡፡

ስትራቴጂዎች

  • ህብረተሰቡን በብድርና ቁጠባ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ማድረግ፣
  • የድኃ ድኃ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በልዬ ትኩረት የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
  • የሴቶችንና ወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ልዬ ትኩረት መስጠት፣
  • ቁጠባን ከብድር ጋር አስተሳስሮ ከባህላዊው ወደ ዘመናዊ በማሸጋገር  ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣
  • ለተለያዬ ቴክኖሎጅዎች ብድር በማቅረብ ምርትና ማሳደግ ናቸው፡፡

ዕሴቶች

  • ታማኝነት፡- ደንበኞች ከተቋሙ በሚያገኙት አገልግሎቶች ራሳቸውን እንዲለውጡ፣ የሚያገኙትን ብድር ለተገቢው አገልግሎት እንዲያውሉ፣ ወጭ ቆጣቢ ሆነው በሚታወቁ እና ተቀባይነት ባላቸው የስራ መስኮች ብቻ እንዲሰማሩ በታማኝነት እናገለግላለን፡፡
  • የአገልግሎት ጥራት፡- ምቹ፣ ፈጣን፣ ውጤታማ፣ አከባቢን የሚመስሉ አገልግሎቶችን ቀርፀን ለደንበኞቻችን እናቀርባለን፡፡
  • ግልፀኝነት፡- ለደንበኞቻችን ግልፅ እና ሙሉ የአሰራር መረጃዎችን በመስጠት ያሉንን ምርት እና አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ተግተን እንሰራለን፡፡
  • ፍትሃዊነት፡- በስነ-ምግባር ታንፀን፣ በደንበኛ በአክባሪነት መልካም ተግባቦትን በማስፈን በፍትሃዊነት ማህበረሰባችንን እናገለግላለን፡፡
  • ሚስጥር ጠባቂነት፡- የማንኛውንም ደንበኛ የግል መረጃ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ባለመስጠት የደንበኞችን የግል   ምስጥር በጥብቅ እንጠብቃለን፡፡
  • ከአድልዎ ነፃ፡- ሁሉም ደንበኞች የተቋሙ ሃብት እና አቅም መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም ደንበኞችን ያለአድልዎ እናገለግላለን፡፡