የፍላጎት ቁጠባ፡-

የፍላጎት ቁጠባ ለነገ የተሻለ ህይወትና ለውጥ፣ የገንዘባቸውን ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ፣ ተጨማሪ ወለድ ሊያገኙበት ይረዳ ዘንድ ተለያዩ የስራ መስክ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ የመንግስት ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት፣ ገቢ ሰብሳቢ የሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የተለያዩ የዕምነት ተቋማት፣ የተለያዩ የስራ መስክ ላይ የተሰማሩ ማህበራት፣ ታዳጊ ህፃናት የዚህ ቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

የፍላጎት ቁጠባ አይነቶች፡- የፍላጎት ቁጠባ በሙዳይ ሳጥን ወይም በቀጥታ በቁጠባ ደብተር ላይ መቆጠብ የሚቻል ሲሆን በጊዜ ገደብ እና ያለጊዜ ገደብ በየትኛውም ሰዓት በደንበኛው ፍላጎትና የወጪ ጥያቄ መነሻ ወጪ መሆን የሚችል ሊቆጥቡ ይችላል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ለቆጣቢ ደንበኞች በተለያዩ ቅድመ-ሁኔታዎች መነሻ ከ7% እስከ 9% ዓመታዊ ወለድ ይከፍላል፡፡ የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ለቆጣቢ ደንበኞቹ ከዚህ በፊት ሲሰጥ ከነበረው የገንዘብ ደህንነነት አስተማማኝ ዋስትና በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ቁጠባ መድን ፈንድ አባል ተቋም በመሆን “መነሻ ዓረቦን” እና “ዓመታዊ ዓረቦን” ክፊያ በማጠናቀቅ ደንበኞች ያለምንም ስጋት በተቋሙ እንዲቆጥቡ ተጨማሪ ዋስትና ለደንበኞቹ ገብቶላቸዋል፡፡