ስያሜ
የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም
የተቋሙ ዓላማ
- በግብርናና ከግብርና ውጭ ለሚደረገው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የብድር አገልግሎት መስጠት፣
- የደሃውን ህዝብ ካፒታል በማሳደግ እና ገቢውን በማብቃቃት የመቆጠብ ባህሉእንዲዳብር ማድረግ፣
- በግለሰቦች ዕጅ ያለስራ ተበታትኖ የሚገኘውን ገንዘብ በቁጠባ በማሰባሰብ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎችንየብድር አገልግሎትበማቅረብና ተጠቃሚ በማድረግ ከድህነት ማላቀቅ፣
- የብድር አቅርቦት በመስጠት ህብረተሰቡን ከአራጣ አበዳሪዎች ብዝበዛ ነፃ ማውጣት፣
የተቋሙ ራዕይ
- ልማታዊ አመለካከቱ የላቀ፣ በብድር አጠቃቀሙ ውጤታማ የሆነ፣ የቁጠባ ባህሉ የዳበረ፣ ከድህነት የተላቀቀ እና በእራሱ የሚተማመን ደንበኛ (ዜጋ) ማየት ነው ፡፡
- በዝቅተኛ እና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ አምራች የህብረተሰብ ክፍሎች በዘላቂነት የብድርና የቁጠባ አገልግሎት አግኝተው ኢኮኖሚያዊ ገቢያቸው እንዲያድግ፣ ኑሯቸው እንዲሻሻል ብሎም ድህነት እንዲቀረፍ ማገዝ ነው፡፡
የተቋሙ ስትራቴጂዎች
- ህብረተሰቡን በብድርና ቁጠባ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ማድረግ፣
- የድኃ ድኃ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በልዬ ትኩረት የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
- የሴቶችንና ወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ልዬ ትኩረት መስጠት፣
- ቁጠባን ከብድር ጋር አስተሳስሮ ከባህላዊው ወደ ዘመናዊ በማሸጋገር ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣
- ለተለያዬ ቴክኖሎጅዎች ብድር በማቅረብ ምርትና ማሳደግ ናቸው፡፡
የተቋሙ ዕሴቶች
- ታማኝነት፡- ደንበኞች ከተቋሙ በሚያገኙት አገልግሎቶች ራሳቸውን እንዲለውጡ፣ የሚያገኙትን ብድር ለተገቢው አገልግሎት እንዲያውሉ፣ ወጭ ቆጣቢ ሆነው በሚታወቁ እና ተቀባይነት ባላቸው የስራ መስኮች ብቻ እንዲሰማሩ በታማኝነት እናገለግላለን፡፡
- የአገልግሎት ጥራት፡- ምቹ፣ ፈጣን፣ ውጤታማ፣ አከባቢን የሚመስሉ አገልግሎቶችን ቀርፀን ለደንበኞቻችን እናቀርባለን፡፡
- ግልፀኝነት፡- ለደንበኞቻችን ግልፅ እና ሙሉ የአሰራር መረጃዎችን በመስጠት ያሉንን ምርት እና አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ተግተን እንሰራለን፡፡
- ፍትሃዊነት፡- በስነ-ምግባር ታንፀን፣ በደንበኛ በአክባሪነት መልካም ተግባቦትን በማስፈን በፍትሃዊነት ማህበረሰባችንን እናገለግላለን፡፡
- ሚስጥር ጠባቂነት፡- የማንኛውንም ደንበኛ የግል መረጃ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ባለመስጠት የደንበኞችን የግል ምስጥር በጥብቅ እንጠብቃለን፡፡
- ከአድልዎ ነፃ፡- ሁሉም ደንበኞች የተቋሙ ሃብት እና አቅም መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም ደንበኞችን ያለአድልዎ እናገለግላለን፡፡