ከጭቃ ውስጥ ወርቅ አግኝተናል፤ በ2016 -17 ዓ.ም የፕላስቲክ መልሶ ማምረቻ ቴክኖሎጂ (ኢንዱስትሪ) ወደ ክልሉ ለማስገባት ዕቅድ አለን፡፡” አቶ ጀምበሩ ተሰማ።

“ከጭቃ ውስጥ ወርቅ አግኝተናል፤ በ2016 -17 ዓ.ም የፕላስቲክ መልሶ ማምረቻ ቴክኖሎጂ (ኢንዱስትሪ) ወደ ክልሉ ለማስገባት ዕቅድ አለን፡፡” አቶ ጀምበሩ ተሰማ።

ስራ ለመጀመር ከሰባት ዓመታት በላይ በዕቅድና ጥናት ላይ የነበሩ፣ የማህበሩ ዓባላት ተምረው ተመርቀው ለዓመታት ስራ አጥ የነበሩ፣ “ጀንበሩ፣ ዮዲትና ጓደኞቻቸው” ኢንተርፕራይዝ በአሶሳ ከተማ ያደራጁ፣ በ2013 ዓ.ም በ500 ሺ ብር የቡድን ብድር ስራ የጀመሩ፣ በተለምዶ “ቁራሊዮ” በማሰባሰብ እና አጥቦ በመፍጨት ለእንደገና ማምረት (RECYCLING) ዝግጁ አድርገው ወደ አዲስ አበባ የሚልኩ፣ አሁን ላይ የቀን ሰራተኞችን ሳያካትት በኮንትራት የሚሰሩ 12 ሰራተኞችና እስከ አምስት ሺ ብር ወርሃዊ ተከፋዮች 6 ቋሚ ሰራተኞች ያሏቸው ናቸው።

“ስራ ማጣት ከባድ ነው፡፡ ስራን መፍጠር ደግሞ ብልጠት ነው፡፡ ፍላጎትና አቅም ከሃሳብ ጋር ኖሮ በገንዘብ ዕጥረት ምክኒያት ስራ አጥ መሆን ቀላል አይደለም፡፡ ሰው ከሃሳቡ መሞት የለበትም፤ ይልቁንም ሃሳቡን ወደ ተግባር ለመቀየር መፍጨርጨር አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ ልማታዊ የሆነ ዓላማ እንዲኖራቸው ለወጣቶች ይህንን ብዙ ጊዜ ነው የምናገረው፡፡ እኛ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ የቆየን ቢሆንም ከማይጠቅም ጭቃ ውስጥ ማለትም ማህበረሰቡ ተገልግሎ ከሚወረውረው ቆሻሻ ውስጥ ወርቅ አይተናል፡፡ ለዚህም የብድር እና ቁጠባ ተቋም ለስኬታችን ትልቅ ሚና የተጫወተ ባለውለታችን ነው፡፡

ሰው በተለይም ወጣቱ ከውድቀት መማር አለበት፡፡ ድሮም ቢሆን የማይሰራ፣ የማይሞክር፣ የማይፈተን አይወድቅም፡፡ የሚወድቅ ሰው የተፈተነ ነው፡፡ ፈተና ከለለ መውደቅ አይኖርም፡፡ መውደቅም ከለለ መነሳት አይኖርም፡፡ ብዙ ወጣት በትንሽ ሙከራ ተስፋ ይቆርጣል፤ በዚህም ወደ መከረኛ መደበቂያ (ሱስ) ይሄዳሉ፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ከራስ አልፎ ለሌሎች ለመትረፍ ምረን ከመሆን ዕይታን ማስፋት፣ ሃገርንና በተሰቡን እንዲሁም ራሱን መውደድ ያስፈልጋል፡፡ እኛ ራዕያችን ትልቅ ነው፡፡ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም አስፈላጊ አማራጮችን ተጠቅመን በ2016 ዓ.ም Recycle machine ከቻይና እናስመጣለን፡፡ በ2017 ዓ.ም ቅርንጫፎቻችንን በክልሉ አስፍተን ይህንን ስራ ወደ ትልቅ ኢንዱስትሪ ቀይረን ወደ አዲስ አበባና የውጭ ሃገራት የምንልከውን ጥሬ እቃ አስቀርተን እዚሁ ምርቱን እናመርታለን የሚል ዕቅድ አለን” አቶ ጀምበሩ ተሰማ (የማህበሩ ሊቀመንበር)

በ2022/23 እ.አ.አ 414.49 በላይ ቁጠባ በማሰብሰብ ከ 516.3 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር በማሰራጨት በብሄራዊ ባንኩ ስታንዳርድ መሰረት ብድር ለማስመለስ እንደሚሰራ

በ2022/23 እ.አ.አ 414.49 በላይ ቁጠባ በማሰብሰብ ከ 516.3 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር በማሰራጨት በብሄራዊ ባንኩ ስታንዳርድ መሰረት ብድር ለማስመለስ እንደሚሰራ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም የአሶሳ ዲስትሪክት አስታወቀ፡፡

የአሶሳ ዲስትሪክት በአሶሳ ከተማ እና የመተከል ዲስትሪክት በግልገል-በለስ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የ2021/22 እ.አ.አ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2022/23 እ.አ.አ የዕቅድ ማናበብ መድረክ ተጠናቋል፡፡

25-12-2014 ዓ.ም

አሶሳ

የብድር ጥራትን ለማስጠበቅ በደንበኛ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ እና ከአካባቢው የሥራ ባህል ጋር የሚዛመዱ እና ለተቋሙም ሆነ ለደንበኛው ውጤት ማምጣት የሚችሉ አዳዲስ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎቶችን በመቅረጽ በ2022/23 እ.አ.አ 414.49 በላይ ቁጠባ በማሰብሰብ ከ516.3 ሚሊዮን በላይ ብድር በማሰራጨት በብሄራዊ ባንኩ ስታንዳርድ መሰረት ብድር ለማስመለስ እንደሚሰራ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም የአሶሳ ዲስትሪክት አስታወቀ፡፡ ዲስትሪክቱ በ2022/23 እ.አ.አ 112.99 ሚሊዮን አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት ብዙአየሁ እንደተናገሩት የማስፈፀም አቅም ግንባታ፣ የደንበኞች ውጤታማነትን ከምልመላ ጀምሮ በመከታተል፣ ብድርን በቁጠባ ለመሸፈን የሚያስችል ሰፊ ስልት በመንደፍ የብድር ስርጭትን በማስፋት፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር፣ ለእስላሚክ ፋይናንሲንግ አገልግሎት እና ለኮር-ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት በመስጠት በዲስትሪክቱ በዘርፉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አመላክቷል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ም/ ዋና/ ስራ አስፈጻሚ አቶ አድጎ አምሳያ እንደተናገሩት የዲስትሪክቱ ቅርንጫፎች ከፍተኛ የአምራችነት አቅም ያላቸው በተለይም በማዕድን ምርት፣ እርሻ፣ እርባታና ማድለብ፣ የንግድ ሥራ፣ የእንጨት ሥራ፣ ብረታ ብረት ሥራ፣ ምግብ ዝግጅት፣ ኮንስትራክሽን ላይ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በጥንቃቄ በመለየትና ከፍተኛ የፍላጎት ቁጠባ በማሰባሰብ ጥራት እና ተደራሽነት ያለው የብድር ስርጭትን ማስፋት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በሶስቱም ዲስትሪክቶቹ በመታገዝ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎቶችን በማቅረብና የደንበኞችን ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በአጠቃላይ 213.92 ሚሊዮን ብር ገቢ ያገኛ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ተቋሙ አሁን ያለውን 624.9 ሚሊዮን አጠቃላይ ሃብት ወደ አንድ ቢሊዮን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፡፡

በተቋሙ በ2021/22 እ.አ.አ በሁሉም ዲስትሪክቶች በቁጠባ አሰባሰብ፣ ብድር ስርጭት፣ ብድር አመላለስ፣ የውዝፍ ብድር አስተዳደር መሰረታዊ መስፈርቶች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የሸርቆሌ፣ የዳንጉር፣ የኡንዱሉ እና አሶሳ ቅርንጫፎችን በመለየት ዕውቀናና ተጨማሪ የገንዘብ ማበረታቻዎችንም ያበረከተ ሲሆን የአሶሳ ዲስትሪክት ቅርንጫፍ ሰራተኞች የተቋሙ ከፍተኛ የስራ አስፈጻሚ አካላት የዋና መ/ቤቱን የህንፃ ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡

+7