- አትክልቱ ቢያንስ በግማሽ ሄክታር ላይ ያረፈ እና ለምርት የደረሰ መሆን አለበት፡፡
- በቡድን ወይም በግል ተበድሮ የውጤታማነት ታሪክ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- የቋሚ አትክልት ህጋዊ ባለቤትነት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዋስትና ውል ከአካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አትክልቱ እንዳይሸጥ/እንዳይለወጥ/ለ3ኛ ወገን እንዳይተላለፍ የእግድ ደብዳቤ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አትክልቱ አስተማማኝ ጥበቃ የሚደረግለት መሆን አለበት፡፡
- የብድር መጠን ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ሊደርስ ይችላል፡፡
የብድሩን 10% በቅድሚያ ይቆጥባሉ፣ በየወሩ ብየድሩን 1% ይቆጥባሉ፡፡
- የብድሩ መመለሻ ጊዜ ጣሪያው አስከ አንድ ዓመት ነው፡፡
- ማንጎ፣ ቡና፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሙዝ፣ ጌሾ፣ ባህርዛፍ፣ ቀርቅሃ፣ ሸንኮራ አገዳ ቋሚ አትክልት ናቸው፡፡