የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ሰራተኞች እና ማኔጅመንት የዘንድሮውን የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በህብረት እንታገል፡፡”

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ሰራተኞች እና ማኔጅመንት የዘንድሮውን የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በህብረት እንታገል፡፡” በሚል መሪ ቃል ከክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በፖናል ዉይይት አክብሯል።

ቤ/ጉ/ብድር እና ቁጠባ ተቋም ማኔጅመንት፣ የአሶሳ ዲስትሪት እና የቅርንጫፎቹ ስራ አስኪያጆች የአመራር እና የደንበኛ አያያዝ ክህሎት ስልጠና

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ማኔጅመንት፣ የአሶሳ ዲስትሪት እና የቅርንጫፎቹ ስራ አስኪያጆች የአመራር እና የደንበኛ አያያዝ ክህሎት ስልጠና በቢዝነስ ደቨሎፕመንት እና ሪሰርች ስራ ክፍል በመታገዝ ሰሞኑን ወስደዋል።

የተሻለ የአመራር ቁርጠኝነት በማስፈን፣ አውንታዉ የአመለካከት ለውጥ በማምጣት፣ የዳበረ የባለቤትነት ስሜት በማጎልበት፣ የተሻለና ዉጤታማ የደንበኛ አያያዝ በማስፈን የላቀ የጋራ ዉጤት ከማስመዝገብ አኳያ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት ስልጠናው የሚያግዝ ነው ተብሎ ይጠበቃል።

የዋና መ/ቤት የህንፃ ግንባታ ሂደት

በየደረጃው ያላችሁ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ሁሉም ስራ አስኪያጆች የ2022/23 ዓመታዊ የስራ እንቅስቃሴ ሪፓርታችሁን ከማስተቸት እና አዲስ አመታዊ ዕቅዳችሁን ከመቀበል ጎን ለጎን የሁላችንም የስራ ውጤት የሆነውን የዋና መ/ቤት የህንፃ ግንባታ ሂደት ስለጎበኛችሁ እናመሰግናችኋለን። በጉብኝታችሁ ወቅት የሰጣችሁን ገንቢ አስተያየት እና የተሰማችሁ ልባዊ ደስታ ለሁላችንም ለነገው የተቀናጀና የተሻለ ስራ ስንቅ ነው።

ተቋሙ ለደንበኞቹ እና ለሰራተኞቹ አስተማማኝ እና ምቹ የአገልግሎት መስጫ እና መቀብያ ቦት በሁሉም ቅርንጫፎቹ የማመቻቸት ግዴታ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት የረጅም እና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያለው ስለሆነ ወደ ፊት እናንተም አገልግሎት በምትሰጡባቸው አከባቢዎች ወጥ በሆነ ዲዛይን መለስተኛ ግንባታዎችን መስራት የሚያስችል አቅም የመፍጠር ጉዳይ ላይ ትኩረት እንድታደርጉ አደራ ማለት እንፈልጋለን።

ዓመቱ የስኬት ይሁንልን!

የ2022/23 የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ግምገማ እና እ.አ.አ የ2023/24 ዕቅድ እያናበበ ይገኛል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ከዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎቹ ጋር በመሆን በአሶሳ ከተማ እ.አ.አ የ2022/23 የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ግምገማ እና እ.አ.አ የ2023/24 ዕቅድ እያናበበ ይገኛል።

የተቋማችን ደንበኛ አቶ ሁሴን አልሃሰን ከተቋማችን ባገኙት የብድር አገልግሎት በኡራ ወረዳ ፉለደሩ ቀበሌ በዘንድሮው ምርት ዘመን እየሰራችሁ ባለው ውጤታማ የግብርና ስራ

የተቋማችን ደንበኛ አቶ ሁሴን አልሃሰን ከተቋማችን ባገኙት የብድር አገልግሎት በኡራ ወረዳ ፉለደሩ ቀበሌ በዘንድሮው ምርት ዘመን እየሰራችሁ ባለው ውጤታማ የግብርና ስራ እና እንደአጠቃላይ እያስመዘገቡ ባሉት ውጤት ተቋሙ ይኮራብዎታል። የእርስዎን አይነት ደንበኛ ማገልገል ኩራት ነው።