ከጭቃ ውስጥ ወርቅ አግኝተናል፤ በ2016 -17 ዓ.ም የፕላስቲክ መልሶ ማምረቻ ቴክኖሎጂ (ኢንዱስትሪ) ወደ ክልሉ ለማስገባት ዕቅድ አለን፡፡” አቶ ጀምበሩ ተሰማ።

“ከጭቃ ውስጥ ወርቅ አግኝተናል፤ በ2016 -17 ዓ.ም የፕላስቲክ መልሶ ማምረቻ ቴክኖሎጂ (ኢንዱስትሪ) ወደ ክልሉ ለማስገባት ዕቅድ አለን፡፡” አቶ ጀምበሩ ተሰማ።

ስራ ለመጀመር ከሰባት ዓመታት በላይ በዕቅድና ጥናት ላይ የነበሩ፣ የማህበሩ ዓባላት ተምረው ተመርቀው ለዓመታት ስራ አጥ የነበሩ፣ “ጀንበሩ፣ ዮዲትና ጓደኞቻቸው” ኢንተርፕራይዝ በአሶሳ ከተማ ያደራጁ፣ በ2013 ዓ.ም በ500 ሺ ብር የቡድን ብድር ስራ የጀመሩ፣ በተለምዶ “ቁራሊዮ” በማሰባሰብ እና አጥቦ በመፍጨት ለእንደገና ማምረት (RECYCLING) ዝግጁ አድርገው ወደ አዲስ አበባ የሚልኩ፣ አሁን ላይ የቀን ሰራተኞችን ሳያካትት በኮንትራት የሚሰሩ 12 ሰራተኞችና እስከ አምስት ሺ ብር ወርሃዊ ተከፋዮች 6 ቋሚ ሰራተኞች ያሏቸው ናቸው።

“ስራ ማጣት ከባድ ነው፡፡ ስራን መፍጠር ደግሞ ብልጠት ነው፡፡ ፍላጎትና አቅም ከሃሳብ ጋር ኖሮ በገንዘብ ዕጥረት ምክኒያት ስራ አጥ መሆን ቀላል አይደለም፡፡ ሰው ከሃሳቡ መሞት የለበትም፤ ይልቁንም ሃሳቡን ወደ ተግባር ለመቀየር መፍጨርጨር አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ ልማታዊ የሆነ ዓላማ እንዲኖራቸው ለወጣቶች ይህንን ብዙ ጊዜ ነው የምናገረው፡፡ እኛ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ የቆየን ቢሆንም ከማይጠቅም ጭቃ ውስጥ ማለትም ማህበረሰቡ ተገልግሎ ከሚወረውረው ቆሻሻ ውስጥ ወርቅ አይተናል፡፡ ለዚህም የብድር እና ቁጠባ ተቋም ለስኬታችን ትልቅ ሚና የተጫወተ ባለውለታችን ነው፡፡

ሰው በተለይም ወጣቱ ከውድቀት መማር አለበት፡፡ ድሮም ቢሆን የማይሰራ፣ የማይሞክር፣ የማይፈተን አይወድቅም፡፡ የሚወድቅ ሰው የተፈተነ ነው፡፡ ፈተና ከለለ መውደቅ አይኖርም፡፡ መውደቅም ከለለ መነሳት አይኖርም፡፡ ብዙ ወጣት በትንሽ ሙከራ ተስፋ ይቆርጣል፤ በዚህም ወደ መከረኛ መደበቂያ (ሱስ) ይሄዳሉ፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ከራስ አልፎ ለሌሎች ለመትረፍ ምረን ከመሆን ዕይታን ማስፋት፣ ሃገርንና በተሰቡን እንዲሁም ራሱን መውደድ ያስፈልጋል፡፡ እኛ ራዕያችን ትልቅ ነው፡፡ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም አስፈላጊ አማራጮችን ተጠቅመን በ2016 ዓ.ም Recycle machine ከቻይና እናስመጣለን፡፡ በ2017 ዓ.ም ቅርንጫፎቻችንን በክልሉ አስፍተን ይህንን ስራ ወደ ትልቅ ኢንዱስትሪ ቀይረን ወደ አዲስ አበባና የውጭ ሃገራት የምንልከውን ጥሬ እቃ አስቀርተን እዚሁ ምርቱን እናመርታለን የሚል ዕቅድ አለን” አቶ ጀምበሩ ተሰማ (የማህበሩ ሊቀመንበር)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *