- ቋሚ የሆነ የቆርቆሮ መኖሪያ ቤት ያለው፡፡
- የቋሚ መኖሪያነት ህጋዊ ማረጋገጫ ማቅረብ፡፡
- ደንበኞች ዕዳ የለለባቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ደንበኞች በቂ የቁም ከብቶች ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ደንበኞች የስራ ቦታ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ደንበኞች የመስራት ቁርጠኝነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ብድሩን ለመክፈል የሚያስችል አስተማማኝ ገቢ መኖር አለበት፡፡
- ደንበኞች የብድሩን 25 % በቅድሚያ መቆጠብ አለባቸው፡፡
- የብድር ጣሪያ ለሶላር እስከ 30 ሺ ብር ሲሆን ለባዮጋዝ ደግሞ አስከ 20 ሺ ብር ነው፡፡
- በከተማ ቤት ወይም በመንግስት ሰራተኛ ወይም በቡድን ዋስትና የሚሰጥ ብድር ነው፡፡
- የብድር መክፈያ ጊዜ በየ3 ወይም 6 ወሩ የሚከፈል ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ተጠቃሎ መከፈል አለበት፡፡
- ሴቶችና ሞዴል አርሶ አደሮች ይበረታታሉ፡፡