“ከ500 ብር ጀምሮ በዕቁብ መልክ በቡድን በቆጠብነው 50 ሺ ብር ዋስትና ተነስተን ዛሬ ባለ-ሃብት እየተባልን ነው፡፡ አልሃምዱሊላህ ከዚህ በላይ እናድጋለን፡

“ከ500 ብር ጀምሮ በዕቁብ መልክ በቡድን በቆጠብነው 50 ሺ ብር ዋስትና ተነስተን ዛሬ ባለ-ሃብት እየተባልን ነው፡፡ አልሃምዱሊላህ ከዚህ በላይ እናድጋለን፡፡ ህብረተሰቡ ሲጠቀም እንደወጣት እኛም እናድጋለን፡፡” አቶ ሁሴን አልሂሰን (በኡራ ወረዳ የባሻቡዳ ቀበሌ ነዋሪ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድርና ቁጠባ ተቋም የአሶሳ ቅርንጫፍ ደንበኛ)

ቀደም ሲል በሹፍርና ሙያ ይተዳደር የነበረ፣ 50 ሺ ብር ቆጥቦ ከ250 ሺ ብር ጀምሮ የአሶሳ ቅርንጫፍ የቡድን ብድር ደንበኛ የሆኑ፣ በወሰዱት ብድር ስርተው የእርሻ ትራክተር እና የእህል ወፍጮ ባለቤት የሆኑ፣ በአሁኑ ሰዓት በቀን ከ18 በላይ ሰራተኛ የሚያሰራ 5 ዓባላት ያሉት አልሂሰን፣ መሪየምና ጓደኞቹ የሚባል የእርሻ ስራ ማህበር ያደራጁ ናቸው።

“የስኬታችን ሚስጥር ፅናትና ብርታት ነው፡፡ ብድሩን ለጫት፣ ለሲጋራ፣ ለጠላ ቤት አላዋልነም፡፡ የስራ እንጂ የሻይ ሱስ እንኳን የለብንም፡፡ ማህበራችንን አልበተንነም፣ ገንዘብ አልተከፋፈልነም፣ ወጪ እንጂ አስተማማኝ ገቢ የለለውን ሞተር ሳይክል እንኳን አልገዛንበትም፡፡ እኛ የገዛነው የግብርና ግብዓት ነው፡፡ ከዚያም በ20 ሺ ብር ትራክተር ተከራይተን 8 ሄክታር አለማን፡፡ በ8 ሄክታር ያለማነው ፍሬ ሲያፈራ ትራክተር ገዛን፡፡ የወሰድነውን ብድር ለስራ ዓላማ ነው ያዋልነው፡፡ የማህበረሰባችን ጥያቄ የነበረው የዕህል ወፍጮም ገዝተን አገልግሎት እየሰጠ ነው።

በመጀመሪያ ዙር ትራክተር ገዝተናል፡፡ በገዛነው ትራክተር በዚህ ዓመት በ17 ሄክታር ላይ ያመረትነው አኩሪአተር፣ በቆሎ፣ በርበሬ፣ ማሽላ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ ነው፡፡ ከበርበሬ ምርት ብቻ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ገቢ እንጠብቃለን፡፡ አልሃምዱሊላህ በደንብ ነው ያፈራልን፡፡ ማሽላ በ8 ሄክታር ላይ ዘርተናል፡፡ ከዚህም ከ400 ኩንታል በላይ እንጠብቃለን፡፡

ወጣቱ ጫት፣ ሺሻ፣ ሲጋራ መተው አለበት፣ የቀደሙት በተለይም ወላጆቻቸው የሚናገሩትን መስማት አለባቸው፡፡” ( አቶ ሁሴን አልሂሰን የማህበሩ ሊቀመንበር)

+3

All reactions:

88Guteta Birhanu, Amuna Asemani and 86 others

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *