- በቡድን ብድር የውጤታማነት ታሪክ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ብድሩን የሚያውሉበት ግልፅ የስራ ዕቅድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የንብረት የዕግድ ደብዳቤ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከሚኖርበት የቀበሌ አስተዳደር ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለዋስትና የሚቀርበው ቆርቆሮ ቤቱ ቢያንስ ከ45 ዚንጎ(ቅጠል) መብለጥ አለበት፡፡
- ንብረቱ ከዕዳ ነፃ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የብድር መጠን ከ25 ሺህ እስከ 100 ሺ ሊደርስ ይችላል፡፡
- የብድሩን 15% በቅድሚያ እና 1% በየወሩ መቆጠብ አለባቸው፡፡
- የብድር ዘመኑ አንድ አመት ነው፡፡