- ህጋዊ የስራ መስክ ላይ የተሰማሩ፣ ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የፀደቀ መተዳደሪያ ደንብ ያላቸው፣ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ህጋዊ የስራ ቦታ ማረጋገጭ ያላቸው፣ ከዕዳ ነፃ የሆነ የንብረት ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፣ የዋስትና ፈንድ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ የቤተሰብ ዋስትና ማቅረብ ለሚችሉ የሚሰጥ ሲሆን ደንበኞች የብድር ጥያቄ ማመልከቻ፣ የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ የብድር መጠየቂያ ቃለ-ጉባኤ፣ የስራ ዕቅድ እና ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ የሚገልፅ ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዚህ ዘርፍ ከ50 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ሊሰጣቸው ይችላል፡፡
- ደንበኞች የብድሩን 20% በቅድሚያ ይቆጥባሉ፡፡
- የብድሩ መመለሻ ጊዜ እንደ ስራው አይነት የሚወሰን ሲሆን የብድር ዘመኑ ሶስት ዓመት ነው፡፡