የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድርና ቁጠባ ተቋም ከአሶሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በክልሉ የብድር አመላለስ ሁኔታን

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድርና ቁጠባ ተቋም ከአሶሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በክልሉ የብድር አመላለስ ሁኔታን አስመልክቶ ያደረገውን የጥናት ውጤት ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።

በመድረኩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድርና ቁጠባ ተቋም ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስራት ብዙአየሁ ተቋሙ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የቁጠባ ባህል በማሻሻል የክልሉን የመልማት አቅም በማሳደግ ረገድ የተሰጠውን ተልዕኮ እየተወጣ ስለመሆኑ አመላክተዋል።

ተቋሙ የአሰራርና የተደራሽነት አድማሱን በማዘመንና በማስፋፋት በ23 ቅርንጫፎቹ እየሰጠ ባለው አገልግሎት አጠቃላይ ሀብቱን ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ማድረሱን ጠቅሰው ህብረተሰቡም በተቋሙ በመቆጠብና በመገልገል ተጠቃሚ እንዲሆን ጠይቀዋል።

የተቋሙ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙሳ አህመድ ተቋሙ ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የብድር አገልግሎት በመስጠትና የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ በቅርበት እያገዘ መሆኑን አስረድተዋል።

ባለድርሻ አካላትም ህብረተሰቡን በማስገንዘብና በተለያየ መንገድ የብድር አመላለስ ችግሮች እንዲፈቱ ከተቋሙ ጎን በመቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በጥናቱ የተቋሙን ደንበኞች የብድር አመላለስ ችግር ለመለየትና ሊወሰዱ የሚገቡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማመላከት የተሄደው እርምጃ ጥሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም የተቋሙን አጠቃላይ አሰራሮችና የደንበኞችን ሁኔታ ባገናዘበ ተጨማሪ ጥናቶች ተደረገው የደንበኞችን ተገልጋይነት ማሳደግና የብድር አመላለስ ስርዓቱን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

ተቋሙ በተሻለ መንገድ ህብረተሰቡን እያገለገለ የሚገኝ አንጋፋ ተቋም እንደመሆኑ ከዚህም በተሻለ ማደግና መስፋት እንዳለበትም ተሳታፊዎቹ አንስተዋል።

በመድረኩም በቀረበው የጥናት ውጤት መነሻነት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይም የተቋሙን የብድር አመላለስ ችግሮች በመሰረታዊነት መቅረፍ እና የደንበኞችን ግንዛቤ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክረ-ሀሳቦች ቀርበውበታል።

ዘገባው የ BGM ነዉ።

One thought on “የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድርና ቁጠባ ተቋም ከአሶሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በክልሉ የብድር አመላለስ ሁኔታን

Leave a Reply to PostMag Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *