የተቋሙ ዓላማ

  • በግብርናና ከግብርና ውጭ ለሚደረገው ኢኮኖሚያዊ  እንቅስቃሴ የብድር አገልግሎት መስጠት፣
  • የደሃውን ህዝብ ካፒታል በማሳደግ  እና ገቢውን በማብቃቃት  የመቆጠብ ባህሉእንዲዳብር ማድረግ፣
  • በግለሰቦች ዕጅ ያለስራ ተበታትኖ የሚገኘውን ገንዘብ በቁጠባ በማሰባሰብ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎችንየብድር አገልግሎትበማቅረብና ተጠቃሚ በማድረግ ከድህነት ማላቀቅ፣
  • የብድር አቅርቦት በመስጠት ህብረተሰቡን ከአራጣ አበዳሪዎች ብዝበዛ ነፃ ማውጣት፣

የተቋሙ ስትራቴጂዎች

  • ህብረተሰቡን በብድርና ቁጠባ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ማድረግ፣
  • የድኃ ድኃ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በልዬ ትኩረት የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
  • የሴቶችንና ወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ልዬ ትኩረት መስጠት፣
  • ቁጠባን ከብድር ጋር አስተሳስሮ ከባህላዊው ወደ ዘመናዊ በማሸጋገር  ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣
  • ለተለያዬ ቴክኖሎጅዎች ብድር በማቅረብ ምርትና ማሳደግ ናቸው፡፡