የቁጠባ አገልግሎት;
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል ቁጠባ ማሰባሰብ ዋነኛው ሲሆን ይህም ዘርፈ-ብዙ ነው፡፡ የፍላጎት ቁጠባ፡- የፍላጎት ቁጠባ አይነቶች፡- የፍላጎት ቁጠባ በሙዳይ ሳጥን ወይም በቀጥታ በቁጠባ ደብተር ላይ መቆጠብ የሚቻል ሲሆን በጊዜ ገደብ እና ያለጊዜ ገደብ በየትኛውም ሰዓት በደንበኛው ፍላጎትና የወጪ ጥያቄ መነሻ ወጪ መሆን የሚችል ሊቆጥቡ ይችላል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ለቆጣቢ ደንበኞች በተለያዩ ቅድመ-ሁኔታዎች መነሻ ከ7% እስከ 9% ዓመታዊ ወለድ ይከፍላል፡፡ የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ለቆጣቢ ደንበኞቹ ከዚህ በፊት ሲሰጥ ከነበረው የገንዘብ ደህንነነት አስተማማኝ ዋስትና በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ቁጠባ መድን ፈንድ አባል ተቋም በመሆን “መነሻ ዓረቦን” እና “ዓመታዊ ዓረቦን” ክፊያ በማጠናቀቅ ደንበኞች ያለምንም ስጋት በተቋሙ እንዲቆጥቡ ተጨማሪ ዋስትና ለደንበኞቹ ገብቶላቸዋል፡፡
የብድር አገልግሎት;
ሀ. አሁናዊ የብድር አገልግሎቶች፡- የግብርና ግብዓት አቅርቦት ብድር /የግብዓት እና የእርሻ በሬ ግዥ/ የደሞዝ ዋስትና ብድር /የመንግስት ሰራተኞች ብድር / በመደበኛ ጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁት የሚሰጥ ብድር ለጥቃቅን ንግድ የሚሰጥ ብድር የቋሚ አትክልት ዋስትና ብድር የተቋማት /ማህበራት/ ብድር መንግስት ሰራተኞች የቤት ግንባታ ብድር፣ የባዮጋዝ እና ሶላር ሃይል ማመንጫ ብድር፣
ከወለድ ነፃ አገልግሎት
ከወለድ ነፃ አገልግሎት BGCSI ልዩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ፋይናንስ እና የቁጠባ ምርቶችን ያቀርባል ባንኩ የፋይናንሺንግ ምርት ያለው በሙራባሃ ኢስቲና ስላም እና ከረድ የቁጠባ ምርቶች ዋዲያህ ሶፌ ማቆየት አካውንት ያልተገደበ የሞዳራባ ኢንቨስትመንት አካውንት እና የውጭ ምንዛሪ ተቀማጭ ሂሳብ ናቸው።